በአዲስ አበባ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12 ቀን 2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።
የቦርዱ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በመዲናዋ የምርጫ ቁሳቁስ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ የምርጫ ክልሎች እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል።
ምርጫ በሚካሄድባቸው ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከቁሳቁስ ስርጭት ጋር በተያያዘ በሁሉም አካባቢዎች እስካሁን ያጋጠመ ችግር አለመኖሩንም ጠቅሰዋል።