ቀጥታ፡

በስዊዘርላንድ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገቡ ጫናዎችን በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ

ሰኔ 10 /2013 (ኢዜአ) በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ያልተገቡ ጫናዎችን በመቃወም በጄኔቭ ከተማ ሰልፍ አደረጉ።

በወቅቱ ሰልፈኞቹ ካስተጋቧቸው መልዕክቶች መካከል ‘በኢትዮጵያ ላይ የምታሳድሩትን ያልተገባ ጫና አቁሙ’፣ ‘ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባዎቻችሁ ሚዛናዊነትን የጠበቁ ይሁኑ’፣ ‘የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም’ የሚሉት የሚገኙበት ይገኙበታል።

በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ወዳጅነት ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ለውጥ እንዲደግፍ እና የሰብአዊ እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሰልፉን ያስተባበሩት የአውሮፓና ስዊዘርላንድ ‘ዲፌንድ ኢትዮጵያ’ ግብረ ሃይል አባላት ሲሆኑ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ደብዳቤም በወቅቱ በስፍራው ለተገኙት የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆ ባይደን እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን በጄኔቭ ከተማ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ማስገባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም