የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሰኔ 10/2013 የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ለሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊነት ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ደጋፊዎችና አጠቃላይ ህዝቡ ሰላማዊነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
ሁሉም አካላት ግጭት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ድርጊቶች በመጠንቀቅ ምርጫው በሰላም እንዲከናወን ጉልህ ሃላፊነት አለባቸው ብሏል ጉባኤው በመግለጫው።
ከተፎካካሪዎች በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን በተለይ ወጣቶች ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ከምርጫው በኋላም ውጤቱ በሚመለከተው አካል እስከሚገለፅ ድረስ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫዎች ሚናፈሱ ወሬዎች ሊደናገሩ አይገባም ብለዋል።