በትግራይ 4ሺህ 400 ኩንታል የአርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች ተያዙ - ኢዜአ አማርኛ
በትግራይ 4ሺህ 400 ኩንታል የአርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች ተያዙ
መቀሌ ሰኔ 10/2013 (ኢዜአ) በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች በእርዳታ የቀረበ 4ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ አየር በአየር ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች መያዛቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰው ለኢዜአ እንደገለፁት ለተፋናቃዮች የመጣ የእርዳታ እህል ሰሞኑን አየር በአየር ለመሽጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስምንት ሰዎች ተይዘዋ።
ግለሰቦቹን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጠርጣሪ ግለሰቦቹ እጅ የነበረ የእርዳታ ስንዴን ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲከፋፈል መደረጉን አመልክተዋል።
“ለተፈናቃይ ወገኖች የቀረበ የእርዳታ ስንዴ ዘርፎ ለግል ጥቅም ለማወዋል መሞከር አፀያፊ ነው” ያሉት ሀላፊው በእርዳታ የሚቀርብ እህል በአግባቡ ለተፈናቀሉ እንዲደርስ ሁሉም በንቃት ሊከታተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።