በኢትዮጵያ ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝትን በማዘውተር እንደሚገባ ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝትን በማዘውተር እንደሚገባ ተገለጸ
ሰኔ 9 /2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝት (ሃይኪንግ)ን በማዘውተር ከዘርፉ የሚገኘውን በርካታ ጠቀሜታዎች መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ ።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ሰራተኞች ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝት (ሃይኪንግ) በጉለሌ እጽዋታ ማዕከል አካሂደዋል።
በዚህ ጉብኝት 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜተር የሸፈነ የእግር ጉዞ ነው አድርገዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም ካሳሁን የሀገር ውስጥ ጉብኝት ባህልን ለማዳበር የተለያዩ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነ ተናገራዋል።
ሃይኪንግ /ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝት/ ቱሪዝምን ለማበረታታት እንደሚያግዝም ነው የተናገሩት።
ተራራን የመውጣትና የእግር ጉዞ ጉብኝት ለማሳደግ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ስራዎች መጀመራቸውንም ነው የተናገሩት።
ቱሪዝም ኢትዮጵያ ሰራተኞች ዛሬ ያደረጉት ጉዞም ሌሎች መሰል ተቋማትና ድርጅቶች መሰል ጉዞ እንዲያደረጉ አርእያ ለመሆን ነው ብለዋል።
በዚህ ጉብኝት ላይ የተገኙት የአልፋ አልፋ አስጎብኝ ድርጅት ባለቤት ወጣት ዘላለም ብርሃኑ ሃይኪንግ በአብዛኛው ፈተኛ የሆኑ ተራሮችን በእግር ጉዞ የሚደረግበት ነው ብለዋል።
በዚህ ጉዞም በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረግ በመሆኑ የአካባቢውም ማህበረሰብ ባህልና አኗኗር ለማወቅ ትልቅ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በእግር ጉዞ ወቅት ጤናን በመጠበቅ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላል የሚያስችል ነው ብለዋል።
ይህንና ሌሎች ጠቀሜታዎችን ያለውን ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝት በማሳደግ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመሆኑም የሌሎችም ተቋማት ሰራተኞች መሰል ጉዞ እንዲካሂዱ መክረዋል።
ተራራን የመውጣት የእግር ጉዞና ጉብኝት በተለይም በካናዳ እና አሜሪካ በስፋት የሚዘወተር መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።