በጅማ ከተማ የአዌቱ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል

73

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 08 ቀን 2013 (ኢዜአ) በጅማ ከተማ የአዌቱ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።

የጅማ ከተማን አቆራርጦ የሚያልፈው የአዌቱ የወንዝ የቆሻሻ መጣያ በመሆኑ አካባቢው ለእይታ የማይማርክ ከመሆኑም በላይ ለመጥፎ ሽታ የተጋለጠ ሆኖ ቆይቷል።

የጅማ ከተማ አስተዳደር ወንዙን በማልማትና የመዝናኛ ስፍራ ለማድረግ 47 ሚሊዮን ብር በበመደብ ላለፉት አምስት ወራት ስራውን አከናውኖ አጠናቋል።

ፕሮጀክቱ ለመዝናናት ምቹ በሆነና ማራኪ ሆኖ በመገንባቱ በነገው እለት ለምረቃ ተዘጋጅቷል።

የፕሮጀክቱ መገንባት ለከተማዋ ውበትና በተለይም ለወጣቶች መዝናኛነት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት ከ200 በላይ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም