የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በአምቦ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በአምቦ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ
አዲስ አበባ ሰኔ 8/2013/ኢዜአ/ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በአምቦ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ።
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ከቀናት በኋላ የሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ፍትሃዊ፣ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ዜጎች ድምጻቸውን ለብልጽግና ፓርቲ በመስጠት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥና ልማት እንዲያስቀጥሉም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
"በኢትዮጵያን እናልብስ" በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዜጎች የድርሻውን አበርክቶ እንዲያደርጉም ጠይቋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እዲጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
በፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በርካታ የምዕራብ ሸዋ ዞንና የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።