ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ላይ ከፓርቲዎችና የዞን ሃላፊዎች ጋር ተወያየ - ኢዜአ አማርኛ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ላይ ከፓርቲዎችና የዞን ሃላፊዎች ጋር ተወያየ
ሰኔ 6 ቀን 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ላይ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የዞን ሃላፊዎች ጋር ተወያየ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የዞን አስተዳዳሪዎች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
የውይይቱ አጀንዳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔና የምርጫ ቀነ ቀጠሮን በማስመልከት ነው።
በተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ችግር የመራጮች ምዝገባ ያልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች መኖራቸውን ቦርዱ ቀደም ብሎ መግለጹ ይታወሳል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔና ምርጫ ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጿል።
በዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የዞን አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ የፓርቲ አመራሮችና የዞን አስተዳዳሪዎች በተለይም ህዝበ ውሳኔው በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እንዲመራ ቦርዱ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ሰብሳቢዋ ከተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የዞን አስተዳዳሪዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ምላሽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ከጥቂት አካባቢዎች በስተቀር ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዚህ እለት ምርጫ የማይካሄድባቸው አካባቢዎች ደግሞ በሁለተኛው ዙር ማለትም ጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድምፅ የሚሰጥ ይሆናል።