ቀጥታ፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የያዟቸውን አማራጮች እያስተዋወቁ ነው

ሰኔ 5 / 2013 (ኢዜአ) በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች ያቃልላሉ ያሏቸውን አማራጭ ሀሳቦች ለአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እያስተዋወቁ ነው።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ዛሬ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በምርጫው የሚሳተፉ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲገኙ ቢጋበዙም በመድረኩ የተሳተፉት አምስት ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

ግብዣውን ተቀብው በመድረኩ የተገኙት ብልጽግና፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ አዲስ ትውልድ፣ እናት እንዲሁም ህብር ኢትዮጵያ ፓርቲዎች መሆናቸው ታውቋል።

ፓርቲዎቹ የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የያዟቸውን አማራጭ ሀሳቦች እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ተወዳድረው ቢያሸንፉ የወጣቱን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችን ለመፍታት ያስችለናል ያሉትን አማራጭ ሀሳብ አብራርተዋል።

በውይይት መድረኩ ከከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም