በትግራይ ክልል የኮሌራ በሽታ ክትባት ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በትግራይ ክልል የኮሌራ በሽታ ክትባት ተጀመረ
ሰኔ 5/ 2013 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል የኮሌራ በሽታ ክትባት የመስጠት ዘመቻ በመቀሌ ከተማ በይፋ ተጀመረ።
በዘመቻው በትግራይ ክልል 13 ወረዳዎች የሚገኙ 2 ሚሊዮን ነዋሪዎችና ተፈናቃዮችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል።
የኮሌራ በሽታ ክትባት የመስጠት መርሃ ግብሩ ዛሬ በመቀሌ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
ክትባቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ በጋራ ይሰጡታል ተብሏል።
ክትባቱ ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በላይ ለሆኑ ህጻናት የሚሰጥ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓም ባሉት ተከታታይ 6 ቀናት የሚሰጥ ነው።
ሁለተኛው ዙር ክትባትም ከሰኔ ከ15 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ-ም እንደሚሰጥ በክትባት ዘመቻው በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።