የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 02 /2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የቴሌ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ።

የኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች የቴሌ ብር አገልግሎት ከተጀመረ እስካሁን ያለውን እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው።

አገልግሎቱ ከተጀመረ አንድ ወር የተጠጋው የቴሌ ብር አገልግሎት እስካሁን 160 ሚሊዮን ብር እንደተዘዋወረበት ተገልጿል።

በእስካሁኑ ሂደትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቢሲኒያ ባንክ ደንበኞቻቸው ከአካዎንቶቻቸው ወደ ቴሌ ብር ገንዘብ ማዘዋወር የሚችሉበት አሰራር መዘርጋቱ ተገልጿል።

ሌሎች ሱፐር ማርኬቶች፣ የንግድ ተቋማትና የትራንስፖርት ድርጅቶችም ቴሌ ብርን ለመጠቀም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የኮንትራት ስምምነት እየፈረሙ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ለ53 ሚሊዮን ደንበኞቹ የቴሌ-ብር አገልግሎትን በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም