የድምፅ መስጫ ቀን ስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ይጠናቀቃል - ኢዜአ አማርኛ
የድምፅ መስጫ ቀን ስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ሰኔ 2/2013 የድምፅ መስጫ ቀን የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በቀጣይዮቹ ሁለት ቀናት እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ቀን የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት በመጪዎቹ ሁለት ቀናት እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል፡፡
ቦርዱ የምርጫ ስራ የቁሳቁስ ዝግጅት ያለበትን ሁኔታ ለሚዲያ ባለሙያዎች እያስጎበኘ ነው፡፡
የስልጠና ቁሳቁሱ ስርጭት በደረሰባቸው አካባቢዎች ቦርዱ ለ150 ሺህ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
የድምጽ መስጫ የስልጠና ቁሳቁሶቹ በምርጫ ክልል ወደ ተለዩ አካባቢዎች እንደሚሰራጩ ተጠቁሟል፡፡
ከመራጮች ምዝገባ አንጻር የክልል መሪዎች ትብብር እያደገ መምጣቱን ቦርዱ አስታውቋል፡፡
በማጓጓዝ ሂደቱ እስካሁን የገጠመ ችግር አለመኖሩንም እንዲሁ፡፡
የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጫ እለት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፣፡