የጣናበለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጣናበለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው
ባህርዳር፣ ግንቦት 29 /2013 (ኢዜአ) በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣናበለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው።
በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን ዶላር ወጭ ተደርጓል።
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በ2003 አ.ም ግንባታው ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጠናቀቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
በ2010 አ.ም የፋብሪካው ግንባታ ለቻይናው ሲ ኤም ሲ ኢ ኩባንያ በመሰጠቱ ቀሪው ስራ በ14 ወራት ተጠናቆ ዛሬ ለምረቃ በቅቷል።