አምባሳደር ጀማል በከር በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ፋጥማ አብደላ አልዴን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ጀማል በከር በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ፋጥማ አብደላ አልዴን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ ግንቦት 24/2013/ ኢዜአ/ በባህሬን የኢፌዴሪ የቆንስላ ጽ/ቤት መሪ የሆኑት አምባሳደር ጀማል በከር አዲስ ከተሾሙት በባህሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሮ ኤዥያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከሆኑት አምባሳደር ፋጥማ አብደላ አልዴን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በበየነ-መረብ ውይይ አካሂደዋል፡፡
በዚህም አምባሳደር ጀማል በከር በኢትዮጵያና በባህሬን መካከል ያለው ሁለትዮሽ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖኖሚ፣ የማህበራዊና ባህላዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ግንኙነቶች በሚጠናከርበት ዙሪያ ከዳይሬክቴሯ ጋር በጥልቀት ተወያይቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አምባሳደር ጀማል ስለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በመጪው ብሔራዊ ምርጫ እንዲሁም የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል የባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሮ-ኤዥያ ዳይሬክትር አምባሳዳር ፋጥማ አብደላ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለትዮሽና ቀጠናዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆኗ አካባቢያዊና አለም አቃፍ ግንኝነቶች ይበልጥ ለማጠናከር በቅርበት ከአገራችን ጋር ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
በተያያዘም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ፤ መልሶ መቋቋምና የሰበዓዊ ድጋፍ ዙሪያ እየተደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ግንዛቤ መያዛቸውን፤ ከህዳሴ ግድብ ጋር ያሉ ልዮነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ-የሱዳን ድንበር አለመግባባቶች በድርድርና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያለቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በውይይቱም በሁለቱም አገራት የፖለተካ፤ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር እንዲጎለብት፤ የባህል ትስስር እንዲጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በመፈራረም ህጋዊ የሰው ዝውውር እንዲኖር በጋራ ለመስረት መግባበት ላይ ተደርሷል፡፡