በህግ ማስከበር ዘመቻው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
በህግ ማስከበር ዘመቻው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24/2013/ኢዜአ/ በህግ ማስከበር ዘመቻው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና የቆይታ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ።
የማእረግ እድገቱ የተሰጣቸው በመከላከያ የጤና ዋና መመሪያ ለሚገኙ የሰራዊቱ አባላትና አመራሮች ሲሆን ከምክትል አስር አለቃ እስከ ኮሎኔል ማእረግ ተሰጥቷቸዋል።
እድገቱ የተሰጣቸው 39 ሲሆኑ በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡና የቆይታ ጊዜያቸውን የሸፈኑ መሆናቸውን በመከላከያ ጤና ዋና መመሪያ የሰው ሃብትና አገልግሎት መመሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ያሬድ አዳነ ገልጸዋል።
በሰራዊቱ ዘንድ ማዕረግ ዕድገት የስራ ውጤት መለኪያ ሚዛን መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ለበለጠ ስራ እንዲነሳሱ ያደርጋል ብለዋል።
በማእረግ አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ በመከላከያ ሚኒስቴር የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ የመከላከያ ጤና መመሪያ ሃላፊ ጥጋቡ ይልማ፣ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሠማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ተገኝተዋል።