ቀጥታ፡

የአሶሳ ነዋሪዎች የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው

አሶሳ፤ ግንቦት 24/2013 (ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የውጭ አካላት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ወጣቶችና ሴቶች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰልፉ ተሳትፈዋል።

በሰልፉ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከዳር ለማድረስ ያላቸውን ዝግጁነትና ቁርጠኝነት የሚገልጹ መፈክሮችን አንግበው በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

"አሜሪካና ምዕራባዊያን በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ተፈጻሚ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ነጻ ነበርን፤ ነጻነታችንን እናስቀጥላለን፣ አባይን ከመገደብ ማንኛውም ሃይል አይመክተንም" የሚሉ መልዕክቶች ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም