ቀጥታ፡

የአሜሪካው ሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ኢትዮጵያ ገቡ

ግንቦት 23/2013(ኢዜአ) የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የአሜሪካው ሪፐብሊካን ፓርቲ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ኢትዮጵያ መግባታቸው ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑትን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር፣ ጀምስም ኢንሆፍን ወደ ሁለተኛው ቤትዎ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ እላለሁ” ማለታቸውን ከማህበራዊ ገፃቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ሴናተር፣ ጀምስ ኢንሆፍ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን የቪዛ እገዳ አስመልከተው "የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳዎችን እቃወማለሁ'' ማለታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስትን ከሽብርተኛው ድርጅት ሕውሓት ጋር በተመሳሳይ ረድፍ ለማስቀመጥ መሞከር ተቀባይነት የለውም በማለት፤ “የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ሰላማዊ መፍትሔዎችን ለማምጣት እየሰራ ይገኛል፤ ሰላምንና አንድነትን ከማምጣት ውጪ ሌላ አካሄድ አልሄደም” በማለትም ውሳኔውን በመቃወም ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ ገልጸው ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም