በምርጫው ሊከበሩ የሚገባቸው የሰብዓዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በምርጫው ሊከበሩ የሚገባቸው የሰብዓዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ ተደረገ
አዲስ አበባ ግንቦት 23/2013 /ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሊከበሩ ይገባቸዋል ያላቸውን ባለሰድስት ነጥብ የሰብዓዊ መብቶች አጀንዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እያስተዋወቀ ነው፡፡
ከአጀንዳዎቹ መካከል ተጨባጭ የሰብዓዊ መብቶች እርምጃ ቃል ኪዳን፣ ለሰብዓዊ መብቶች በቁርጠኝነት መቆም፣ ምርጫው ለስርዓተ ጾታ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ከግጭት ቀስቃሽና የጥላቻ ንግግርና ከኃይል እርምጃ ሙሉ በሙሉ መቆጠብ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የተዘረዘሩት የሰብዓዊ መብቶች አጀንዳ በምርጫ ወቅት ሊከበሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡
ለዚህም ቦርዱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች በተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡