ቀጥታ፡

የጋምቤላ ወጣቶች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጪ ጣልቃ ገብነት ያወገዙ ሰልፍ ተካሄደ

ጋምቤላ ግንቦት 22/2013 (ኢዜአ)  ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣትና የውስጥ ሰላሟን ለማስጠበቅ የምታደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ የሚደረገውን የውጪ ጣልቃ ገብነት በጽኑ እንደሚያወግዙ የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች በሰልፍ ገለፁ።

የከተማው ወጣቶች ‘‘ድምፃችን ለነጻነታች ’’ በሚል መሪ ሃሰብ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ የውጪ ጣልቃ ገብነቶችን በመቋወም ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል።

ሰልፈኞቹ እኛ ወጣቶች በሀገራችን ጉዳይ አንደራደረም፤ አባይ የእኔ ፣  የእኛ የኢትዮያውን ነው፤ አሜሪካና አውሮፓዎች በሀገራችን ጉዳይ ጣለቃ አይግቡ፤ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል ።

እንዲሁም አባቶች ያቆዩልን ሀገር በእኛ ትቀጥላለች፤ ኢትዮጵያ ሞግዚትነት  አያስፈልጋትም፤ እኛ ወጣቶች የሀገራቸን ሉዓላዊነትን እናሰከብራለን የሚሉ ድምጾችንም በማሰማት ሰላማዊ ሰልፋን አካሂደዋል።

ከሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል ታዳጊ ወጣት ሳሙኤል ወንድይፍራው በሰጠው አሰተያየት አሜሪካ ያደረገችውን የቪዛ ክልክላና ሌሎች የውጪ ሀገራት ጣልቃ ገብነትን ለመቃወም  በሰልፉ ላይ  መገኘቱን ተናግሯል።

‘‘ኢትዮጵያ በወጪ ኃይል ሳይሆን በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተጠበቃ የቆየች ሀገር ናት፤ አሁንም ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ በአንድነት ልንቆም ይገባል ’’ ብሏል ወጣቱ።

’’የአባይ ግድብ  ደማችንና ለማንም አሳልፈን የማንሰጠው ሀብታችን ነው’’ ያለው ደግሞ  ወጣት እስካውት ተስሏች ቶል ነው።

መምህር አበራ ደመና በበኩላቸው  በቅርቡ አሜሪካንና ምዕራባዊን በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፈጠር የሞከሩትን ድርጊት ለመኮነን ሰልፈ መውጣታቸውን ተናግረዋል ።

"የኢትየጵያን ሰላምና እድገት የማይፈልጉ የአሜሪካንና የአውሮፓ ሀገራት ጫና ለመፍጠር ቢሞክሩም በጀግኖች ልጆቿ ሉዓላዊነቷና ነፃነቷ አይደፈረም" ብለዋል።

ለታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ስኬት ከገንዘብ እስከ ህይወት መስዋትነት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ወጣት አችወት ባች  ባስተላለፈው መልዕክት ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣትና የውስጥ የሰላም ችግሮቿን ለመፍታት የምታደረገውን ጥረት ለማሰናከል እየተካሄደ ያለው የውጪ ሀገራትን ጣልቃ ገብነት የሚወገዝ ነው ።

በተለይም አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን በዜጎቸ ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋና ሀገር የማፈረስ ሴራ ባለመገንዘብ አሜሪካ፣  ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረጉት ሙከራ ዓለም አቀፍ መርሆችን የሚቃረን መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቧን ከፍፃሜ በማድረስ ከድህነት ለመውጣትና የውስጥ ሰላሟን ለማስጠበቅ እያደረገች ያለውን እውነታ በመገንዝብ አሜሪካም ሆነች የአውሮፓ ሀገራት ከጎኗ ሊቆሙ  እንደሚገባ አመላክቷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ተማስ ቱት በመልእክታቸው በኢትዮጵያ በቅርቡ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ እንዲሁም የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚታትሩ ኃይሎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በተለይም የውስጥ ባንዳዎች የኢትየጵያን ሰላምና ልማት የማይፈልጉ የውጪ ኃይሎችን በማነሳሰት ሀገሪቱ ከድህነት ለመውጣት የምታደረገውን ጥረት ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱን ለማፈረስ የእየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።

የክልሉ ወጣቶች የሀገሪቱን ሰላምና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ጠንክረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም