ቀጥታ፡

የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል

ግንቦት 19 / 2013 (ኢዜአ) የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚሪ ሊግ ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል።

ዛሬ በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ሻምፒዮኑ አራት ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮንነቱን ቀደም ብሎ ያረጋገጠው ፋሲል ከነማ ከሰበታ ከተማ ጋር ያለምንም ግብ አቻ ሲለያይ፣ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ከታህሳስ ወር ጀምሮ የተካሄደው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ነገ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከነማ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ሲጫወቱ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ጅማ አባጅፋር ከሐዲያ ሆሳዕና ይገናኛሉ።

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ54 ነጥብ በአንደኝነት ሲመራ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው እንደ የቅድመ ተከተላቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ሰበታ ከተማ በ37 ነጥብ አራተኛ ደረጃ የተቀመጠ ሲሆን፣ ሀዋሳ ከተማና ሐዲያ ከተማ በ33 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ናቸው።

አቡበከር ናስር ከኢትዮጵያ ቡና በ29 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪቱን ይዟል።

የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም በ20 ግቦች ይከተላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም