ከ2 ዓመት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው - ኢዜአ አማርኛ
ከ2 ዓመት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው
ግንቦት 18 ቀን 2013 (ኢዜአ) ከሁለት ዓመት በፊት በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት ሊቆምላቸው ነው።
አደጋው የደረሰበት የግምቢቹ ወረዳ ቱሉፈራና አጎራባች ቀበሌዎች ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ አራት ፕሮጀክቶችም ሊተገበሩ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ፅሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር አባ ተሾመ ፍቅሬ እንዳሉት ቦይንግ ኩባንያ ለተጎጂ ቤተሰቦች በሰጠው ድጋፍ መሰረት በኢትዮጵያ ጉዳት የደረሰባቸው 18 ሰዎች ቤተሰቦች አደጋው በደረሰበት ስፍራ ያሉ ነዋሪዎች ላደረጉት ሰብዊነት በስፍራው ሐውልት እንዲሰራ ይሁንታ ሰጥተዋል።
የሰውነት ተምሳሌት የሆናችሁ ነዋሪዎች ከአሳዛኙ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ያደረጉት ክብር አድንቀው፤ አደጋ በደረሰበት ስፍራ ነዋሪዎች በአደጋው ያለፉ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ተጎጂዎች ያደረጉት ተግባር ከቦይንግ በተገኘ ገንዘብ ድጋፍ አምስት አይነት ፕሮጀክቶች እንዲተገበሩም ተወስኗል።
ፕሮጀክቶቹ ባለፉት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት አማካኝት የሚተገበር ሲሆን የፕሮጀክቶችን ክንውን የሚቆጣጠር ከኦሮሚያ ክልልና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተውጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን ተናግረዋል።
ይህ ተግባር በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፈፃሚነት ስራዎች መጀመራቸውንና ገልጸው ፤ፕሮጀክቶችም ሶስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች፣ እያንዳንዳቸው 5 ብሎክ ህንፃዎች ያላቸው ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰራሉ።
አንድ ጤና ኬላ ግንባታና ሰባት ድልድዮችም የፕሮጀክቱ አካል ናቸው ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ጉዳት የደረሰበቫቸው 18 ኢትዮጵያዊያን የመታሰቢያ ሐውልት አደጋው በደረሰበት ስፍራ እንዲቆምላቸው ይደረጋል ነው ያሉት።
ፕሮጀክቶቹም በግቢቹ ወረዳ 4 ቀበሌዎች የሚኖሩ 13 ሺህ 852 አባውራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።
በቦይንግ ኩባንያ 106 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱን ገልጸው ፕሮጀክቶቹ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል።