የመገናኛ ብዙኀን ሚና ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመገናኛ ብዙኀን ሚና ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፡ ግንቦት 17/2013(ኢዜአ) የመገናኛ ብዙኀን ሚና ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የምክክር መድረክና የተፋሰስ ልማት ስልጠና በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ።
የምክክር መድረኩ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት እና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን በጋራ የተዘጋጀ ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ የህዳሴ ግድቡ የምጣኔ ሃብት ነጻነትን የሚፈጥር የሉዓላዊነት መገለጫ ነዉ ብለዋል።
ሀገሪቱ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ ከዉጭ ጫና እንድትወጣና የኅብረተሰቡን ኑሮ ለመቀየር 80 በመቶ የደረሰዉን ታላቁ የህዳሴ ግድብን በአንድነት ማጠናቀቅ ይገባል ነው ያሉት።
ለግድቡ መጠናቀቅ የመገናኛ ብዙኀን ሚና ከፍተኛ ነዉ፤ ለዚህም በተከታታይ ሽፋን በመስጠት ሕዝቡ እንዲደራጅና እንዲጠናከር ብሎም ጥቅሙን እንዲያስከብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል ዶክተር አረጋዊ በርሄ።