ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ያለፉት ሦስት ዓመታት የውሃ፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፍ ዓበይት የስኬት ምዕራፎች ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16/ 2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ዘርፍ መሰረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላት ዜጎች ክብራቸውን የጠበቀ ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ላይ አተኩረዋል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ 56 ሺህ 790 የከተማና ገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታን በማጠናቀቅ 15 ሚሊዮን 287 ሺህ 148 ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል 16 ቢሊዮን ብር የብድር ፋይናንስ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት በማሰባሰብ ለ72 ከተሞች መጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የብድር ፋይናንስ ማቅረብ ተችሏል።

ጊቤ 3 የውሃ ማመንጫ (1,870 ሜዋ)፤ የገናሌ ዳዋ 3 የውሃ ማመንጫ(254 ሜዋ) እና የረጲ የደረቅ ቁሻሻ ማመንጫ (25 ሜዋ) ማጠናቀቅና ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የማመንጨት አቅም 4,466 ሜዋ እንዲሁም 19,746 ኪሜ ጠቅላላ ርዝመት ያላቸው የማስተላለፊያ መስመሮች በሥራ ላይ ይገኛሉ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ (79.3 በመቶ)፤ የኮይሻ የዉሃ ማመንጫ ግድብ (45.8በመቶ)፤ የኮይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ (73.9 በመቶ)፤ የአሉቶ ላንጋኖጂኦተርማል(28.3 በመቶ) የደረሱ ሲሆን፤ ከጎረቤት አገሮች የኃይል ሽያጭ ያሳልጣል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮ-ኬንያ 500 ኪቭ የማስተላለፊያ መስመር 97.8 በመቶ ደርሷል።

ከ875,000 በላይ ዜጎች የግሪድ አገልግሎት ሲያገኙ ከ1100 በላይ የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

የመንግስት ወጭ ቅነሳ ጋር ተያይዞ ችግሮች የነበሩባቸውን ፕሮጀክቶች መፍትሔ በመስጠት 4 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች (የርብ፡የጊዳቦ፡ የመቂ ዝዋይ እና የመገጭ ሰራባ የመስኖ ልማት ፕሮክቶች) ማጠናቀቅ 32 ሺህ 400 ሄ/ር በማልማት 56 ሺህ 946 አርሶአደሮች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

ከለዉጡ በኋላ ግንባታቸው እየተካሄደ የሚገኙ እና ከግንባታ በጨረታ ሂደት ላይ የሚገኙ 8 አዳዲስ (ካሊድዲጆ፡ የላኛውጉደር፡ ጨለጨል፤ወልመል የአጅማጫጫ፡ ወይቦ፡ አንገር፡ ኬጦ) የመስኖ ግድብና የመስኖ አውታሮች ሲጠናቀቁ 52ሺህ 192 ሄ/ርበማልማት104 ሺህ 384 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል።

እንቦጭን ከጣና ሀይቅ ማስወገድ ዘመቻ ከ4 ሺህ 302.94 ሄክታር ዉስጥ 3 ሺህ 56.7 ማስወገድ ተችሏል::

ይህም ከአጠቃላይ 85% ማሳካት አስችሏል(የተሳተፈ የሰው ሀይል 396,943(73.4% ሴቶች) ናቸው ተብሏል ይፋ በሆነው የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፍ ዐበይት የስኬት ምዕራፎች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም