በሶማሌ ክልል አቤቱታ የቀረበባቸው 7 የምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሌ ክልል አቤቱታ የቀረበባቸው 7 የምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም
የዜና ማስተካከያ
ግንቦት 13 /2013 (ኢዜአ) በሶማሌ ክልል ከመራጮች ምዝገባ ሂደት ጋር በተያያዘ አቤቱታ በቀረበባቸው 7 የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ቦርዱ ትናንት በሰጠው መግለጫ የዘንድሮው ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 14 መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ባስታወቀበት ወቅት ምርጫው የማይካሄድባቸውን አካባቢዎች ማስታወቁ ይታወሳል።
የመራጮች ምዝገባ በአግባቡ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ምርጫው እንደማይካሄድ ያስታወቀው ቦርዱ፤ በሶማሌ ክልልም በሰባት የምርጫ ክልል የማይካሄድ መሆኑን አስታውቋል።
ነገር ግን ኢዜአ ዜናውን በሰራበት ወቅት ምርጫ የማይካሄድባቸውን ቦታዎች በተመለከተ በሰራው ዘገባ “ከነዚህ መካከል በሶማሌ ክልል፤ ሃረሪ ክልል፣ መተከል ዞንና ሌሎች የጸጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች በተጠቀሰው ቀን የማይካሄድ መሆኑንም ጠቅሰዋል” ብሏል።
ይህም በሶማሌ ክልል ሙሉ ለሙሉ ምርጫው አይካሄድም የሚል ትርጉም ስለሚሰጥ ኢዜአ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ይጠይቃል።