ኢትዮጵያ ለከብሯና ነፃነቷ የማትደራደር መሆኗን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለከብሯና ነፃነቷ የማትደራደር መሆኗን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ግንቦት 10 / 2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ለከብሯና ነፃነቷ ፍፁም የማትደራደር ሀገር መሆኗን ሁሉም ሊገነበዘው እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት16 ቀን 2013 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ሳምንት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ አስጀምረዋል።
በወቅቱም "ኢትዮጵያ ለከብሯና ነፃነቷ ፍፁም የማትደራደር ታላቅ ሀገር መሆኗን ሁሉም ሊገነበዘው ይገባል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነቶች ውስጥ ደምቃ የምትታይ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ተምሳሌት መሆኗንም አንስተዋል።
ከፍ ብለው የሚታዩ የበርካታ ታሪኮች ባለቤትና ልዩ የተፈጥሮ ፀጋ የተላበሰች በብዙ ማንነቶች የተገመደች ታሪካዊ ሀገር መሆኗንም ገልጸዋል።
"በመሆኑም የእነዚህ ሁሉ መገለጫዎችና ታሪኮች ባለቤት የሆነችውን ሀገር ሁሉም በቅጡ ሊያውቃትና ሊረዳት ይገባል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለከብሯና ነፃነቷ ፍፁም የማትደራደር መሆኗን መሆኗን አስገንዝበዋል።
"የኢትዮጵያን እምቅ ሃብት በጋራ በማልማትና በማሳደግ ሁላችንም ለጋራ ብልፅግና መስራት ይገባናል" ሲሉም ጠይቀዋል።