ዩኒቨርሲቲው በኤሌክትሪክ ሀይል ማስፋፋት እንደ ሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት እያገዘ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ዩኒቨርሲቲው በኤሌክትሪክ ሀይል ማስፋፋት እንደ ሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት እያገዘ ነው
ሆሳዕና፣ ግንቦት 9/2013 (ኢዜአ) ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሪክሪክ ሀይል ማስፋፋት እንደ ሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት አስታወቀ።
ዩኒቨርስቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ በተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 38 ተማሪዎች ትላንት በግልገል ግቤ ቁጥር አንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አስመርቋል ።
በዕለቱ ከተመረቁ ተማሪዎች መካከልም ሶስቱ ሴቶች ናቸው።
በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ በክቡር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሮፖሬት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንደወሰን አበበ እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲው በኤሌክትሪክ ሀይል ኢንጀነሪግ ዘርፍ ባለሙያዎችን ማፍራት መጀመሩ ሀገሪቱ በዘርፉ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት ያስችላል ።
ኮሮፖሬቱ የተቋሙን የሰው ኃይል ልማት ለማሳደግና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከዩንቨርሲቲው ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ በህዳሴ ግድብ የተጀመረውን የልማት ጉዞ ለማሳካት ተቋሙ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነም አመልክተዋል ።
ከእለቱ ተመራቂዎች መካከል አንድነት አበበ በትምህርት ቆይታው ያገኘውን እውቀት በመጠቀም ሀገሪቱ በህዳሴ ግድቡ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማገዝ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
በተመረኩበት መስክ ለሀገሬ የበኩሌን አስተዋጾ ለማበርከት ተዘጋጅቻለሁ" ያለችው ደግም ተመራቂ ወሰኔ በዳሳ ነች።