መቀንጨርን ለመቀነስ ሲተገበር የቆየው ፕሮግራም የተደራሽነት ጥናት ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
መቀንጨርን ለመቀነስ ሲተገበር የቆየው ፕሮግራም የተደራሽነት ጥናት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ ግንቦት 6/2013/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት በጤና ሚኒስቴር እና ግብርና ሚኒስቴር ቅንጅት እ.ኢ.አ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲተገበር የቆየው የህጻናትን መቀንጨር የመቀነስ የተሰራ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡
ጥናቱ ዋና አላማና ተደራሽነት አስመልክቶ ዛሬ በአዳማ ከተማ የተገኘውን ውጤት ለባለድርሻ አካላት ይፋ ተደርገጓል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በአውደ ጥናቱ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት ከጥናትና ምርምር፣ ከሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች እንዲሁም ከላቦራቶሪ አቅም ግንባታ አንጻር ኢንስቲትዩቱ እየሰራ የሚገኘውን በርካታ ስራዎች አሉ፡፡
በጥናቱ ዘርፍ ከተሰሩት ስራዎች አሁን ይፋ የተደረገው የህጻናትን መቀንጨር ለመቀነስ የሚፈትሽ ዳሰሳዊ ጥናት አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ የተካሄደው በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በአጠቃላይ 31 ወረዳዎች ሲሆን የህጻናትን የመቀንጨር ችግር ለመቀነስ በአተገባባሩ እና በተደራሽነቱ ላይ ትኩረት በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ችግሮቹን በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው በጥናቱ ከመመላከቱም በላይ ፕሮግራሙ ቀጣይነት እንዲኖረው በመንግስት ሊደገፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በአውደ ጥናቱ መርሀግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮ፣ የግብርና ቢሮ፣ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እና የአጋር ድርጅት ተወካዮች መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡