ቀጥታ፡

የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል

ግንቦት 6/2013 (ኢዜአ) የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አቀረበ።

በመላው አገሪቱ በክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል።በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል, በሲዳማ ክልል እንዲሁም ሶማሌ ክልል የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ ድምጽ መስጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም