ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምን ጎበኙ

ግንቦት 5፤2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች መገኛ የሆነውን ቢላሉል ሐበሺ የማህበረሰብ ሙዚየምን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

ሙዚየሙ የኢትዮጵያ እስላማዊ ቅርሶችን በመሰብሰብ ለመጠበቅ እና ለማሳየት በማሰብ የተቋቋመ ስለመሆኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡በ2010 ዓ.ም የተቋቋመው ሙዚየሙ የእስላማዊ ታሪክ በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል፣ የኢትዮጵያ እስላማዊ ምሁራን፣ የሙስሊም ሱልጣኔቶች እና መሰል እስላማዊ ታሪኮችን እንደያዘ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ሙዚየሙን ይበልጥ ለማስፋፋት እና በተለይም የጥናትና ምርምር ተቋም እንዲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በተለያዩ ጊዜዎች በመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት መጎብኘቱ ብርታትን እንደሚሰጣቸው የሙዚየሙ ኃላፊዎች ተናግረዋል(ኢብኮ)፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም