1442ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል አከባበር በመላው ኢትዮጵያ ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
1442ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል አከባበር በመላው ኢትዮጵያ ተከበረ
ግንቦት 5፤2013 (ኢዜአ)1442ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በመከበር ላይ ይገኛል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማም የዕምነቱ ተከታዮች፣ የዕምነቱ አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው።
በዒድ አል-ፈጥር በዓል አከባበር ላይ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ዒድሪስን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የእምነቱ ምሁራንና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።