ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ኢድን በማስመልከት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እስልምና እምነት ተከታዮች ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ኢድን በማስመልከት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እስልምና እምነት ተከታዮች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2013 ( ኢዜአ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ በዓልን ለማክበር የሚያግዝ ድጋፍ አደረጉ።
ፕሬዝዳንቷ በዚህ ሳምንት የሚከበረውን የኢድ በዓል ለማክበር የሚያግዙ የተለያዩ የምግብ ድጋፎችን አድርገዋል።
ድጋፉን ያበረከቱት በዛሬው ዕለት በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ ፕሬዝዳንቷ ላበረከቱት የኢድ ድጋፍ አመስግነዋል ።
ፕሬዝዳንቷ የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ያደረጉት ድጋፍ አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸው ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ በመከተል ሰብአዊነታቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ባለፈው ዓመት በረመዳን መሳለሚያ እህል በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገኘት ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።