ቀጥታ፡

25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የማራቶን ሪሌ ውድድር በመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ የበላይነት ተጠናቀቀ

ግንቦት 1/2013 ( ኢዜአ)25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የማራቶን ሪሌ ውድድር በመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ የበላይነት ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይህ ውድድር ዛሬ ጠዋት መነሻና መድረሻውን ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ፍላሚንጎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በማድረግ ተካሂዷል።


የማራቶን ሪሌ ውድድሩ ከእያንዳንዱ ክለብ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በጋራ የተካፈሉበት ነው።


በውድድሩም ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ርቀትና ሴቶች ደግሞ የ5 እና 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ሸፍነዋል።

በዚህም የመከላከያ አትሌቶች ቀዳሚ ሆነው በማጠናቀቃቸው እያንዳንዳቸው የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቶች ሁለተኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው የብር ሜዳሊያ፤ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።

በዚህ ውድድር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢኒያም ምሩጽን ጨምሮ የስፖርቱ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም