የኢፌዴሪ አየር ሀይል በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ጀብድ ለፈጸሙ አባላቱ እውቅናና ማዕረግ ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የኢፌዴሪ አየር ሀይል በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ጀብድ ለፈጸሙ አባላቱ እውቅናና ማዕረግ ሰጠ
ሚያዝያ 29 ፣2013 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ አየር ሀይል በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና በተቋማዊ ሪፎርም መልካም አፈፃፀም ለነበራቸው ለከፍተኛ መኮንኖች ሹመት የምስጋናና እውቅና የመስጠት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
በዚህም 44 ከፍተኛ መኮንኖች፣ 47 መስመራዊ መኮንኖች እና 985 ባለመእረግተኞች በድምሩ 1 ሺህ 79 የተፈቀደላቸውን ማእረግ የሚለስበሱ ሲሆን 47 ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረጋቸውን ለብሰዋል፡፡
የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በአሁኑ ወቅት ከውጭና ከውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሀገሪቱን ለማፍረስ እየሰሩ ቢሆንም ዓላማቸው ግን እንደማይሳካ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።ይህን ለመመከትም አየር ኃይሉ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡