ቀጥታ፡

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ለመቀበል ደማቅ ስነስረአት እየተካሄደ ነው

ሀምሌ 25/2010 4ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ለመቀበል ምእመናን፣ የመከላከያና የፌዴራል ማርሽ ባንዶች በሚያቀርቧቸው ህብረዝማሬ በማጀብ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ  ናቸው፡፡ የኦርቶዶክስ  ሃይማኖት አባቶች ምእመናን፣  የሀገር መከላከያና የፌደራል ማርሽ ባንድ ፣አርቲስቶችን ጨምሮ  ሌሎች  የሚመለከታቸው  አካላት ቦሌ አለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ተገኝተዋል፡፡ በቦታው የሚገኙ ምእመናንም ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ለሁለት ተክፍሎ የነበረው ሲኖዶስ ወደ አንድ መምጣቱ ቤተክርስቲያኗ ለምታድርገው የሃይማኖታዊ አገልግሎትና የሰላም  ስራዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት ለሁለት ተከፍሎ የሀገር ቤትና የውጭ ሲኖዶስ እየተባለ ሲጠሩ የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች ቃለ ውግዘታቸውን አንስተው ሰሞኑን ወደ ዕርቅ መምጣታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ድረስ የቤተ ክርስቲያኗን ቀኖና በጠበቀ መልኩ የአቀባበል ስነ ስርዓቱ ይከወናል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም