በጋምቤላ የምርጫ ነክ ግጭቶችን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ - ኢዜአ አማርኛ
በጋምቤላ የምርጫ ነክ ግጭቶችን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ
ጋምቤላ ሚያzዚያ 19 ቀን 2013 ( ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል ምርጫ ነክ ግጭቶችን ለመከላከል የሚያስችል 13 አባላት የተካተቱበት ግብረ ኃይል ተቋቋመ።
በክልሉ ትናንት በተቋቋመው ግብረ ኋይል በአባልነት ከተካተቱ መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የሴቶች ፌደሬሽንና የጸጥታ አካላት ይገኙበታል።
እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች ማህበር፣ የዚቪክ ማህበራት፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎችና መገናኛ ብዙሀን እንደሚገኙበት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ታጠቅ ተፈራ ለኢዜአ እንደገለጹት ግብረ ኃይሉን ማቋቋም ያስፈለገው ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የግጭት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ነው።
ግብረ ኃይሉ የግጭት ስጋቶች መረጃዎችን አስቀድሞ በመተንተን የመከላከልና ችግሮችም ሲከሰቱ ፈጥነው መፍትሄ እንዳያገኙ የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።