ቀጥታ፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ተጀመረ

ኦሶሳ ፤ሚያዚያ 15/ 2013 (ኢዜአ) አራተኛው ሃገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዛሬ በአሶሳ ተጀመረ።

በፎረሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

"የምሁራን ተሳትፎ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ"  በሚል መሪ ሃሳብ  ፎረሙ እስከ ነገ ይቀጥላል።

ዓላማው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ሀገራዊ ጉዳዮችን ማጠናከር እንደሆነ ተገልጿል።

በአሶሳ ዪኒቨርሲቲ  በተጀመረው  ፎረም የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌስር አፈወርቅ ካሱ እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራልና ክልል  አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም