በአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሳተፉ ስፖርተኞች ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሳተፉ ስፖርተኞች ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል
አዲስ አበባ ሀምሌ 24/2010 በአልጄሪያ በተካሄደው ሶስተኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስና የብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽኖች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር አዘጋጅነት ውድድሩ ከሐምሌ 11 እስከ 21 ቀን 2010 ዓ.ም በአልጀርስ ተካሂዷል። የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 18 በሆኑ ስፖርተኞች መካከል የተካሄደ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ በስድስት የስፖርት ዓይነት የተሳተፈች ሲሆን አጠቃላይ ውድድሩ በ30 የስፖርት አይነቶች ተካሂዷል። አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ካራቴ፣ ብስክሌትና ጠረጴዛ ቴኒስ ኢትዮጵያ የተሳተፈችባቸው የስፖርት አይነቶች ናቸው። በዚሁ መሰረት ውድድሩ ትናንት ፍጻሜውን ሲያገኝ ኢትዮጵያ በ11 ወርቅ፣ ስምንት የብርና ስድስት የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 25 ሜዳሊያ በመሰብሰብ ሰባተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
በብስክሌት ውድድር ሶስት ወርቅ ያገኘችው ሄለን ፍስሀ፣ በቦክስ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው እንዳሻው አላዩና በወርልድ ቴኳንዶ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው ታሪኩ ግርማ በውድድሩ ባገኙት ልምድ ተጠቅመው ከሁለት ዓመት በኋላ በጃፓን ቶኪዮ ኦሎምፒክ አገራቸውን ለመወከል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በውድድሩ ላይ ከተጋጣሚዎቻቸው ያገኙት ተሞክሮ በቀጣይ ውድድሮች ላይ እንደሚረዳቸውና በአጠቃላይ ትኩረት ባልተሰጠባቸው ስፖርቶች ውጤት መምጣቱ ስፖርቶቹ ትኩረት ቢሰጣቸው የተሻለ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ገልጸዋል። የአልጄሪያ የስፖርት ልዑካን ቡድን መሪ አቶ ተፈሪ አላምረው ከሌላው ጊዜ በተሻለ የተደረገው ዝግጅት ለተገኘው መልካም ውጤት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። የቡድን መንፈሱ ጠንካራ መሆን ለውጤቱ ጉልህ ሚና መጫወቱን አመልክተው ለውድድሩ የተደረገው ቅድመ ዝግጅት ለሌሎች ቀጣይ ውድድሮች ተሞክሮ ስለሚሆን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ''የአገራችሁን ስም በማስጠራት ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ላደረጋችሁ ስፖርተኞች እንኳን ደስ አላችሁ'' ብለዋል። ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች ሳይበተኑ ተጨማሪ ስፖርተኞች ተጨምረው ለጃፓን ቶኪዮ ኦሎምፒክ ከወዲሁ ጠንካራ ዝግጅት እንዲደረግ ኦሎምፒክ ኮሚቴው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ርስቱ ይርዳ በበኩላቸው ውጤቱ አበረታችና መልካም ቢሆንም በውጤቱ ሳንዘነጋ ቀጣይ ለሚጠብቁን አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በተለያዩ ስፖርቶች በቶኪዮ ኦሎምፒክ ተሳትፋ ውጤት እንድታመጣ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ከአራት ዓመት በፊት ሁለተኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ በቦትስዋና ርዕሰ-መዲና ጋቦሮኒ ሲካሄድ ኢትዮጵያ 14 የወርቅ፣ ስድስት የብር እና ሰባት የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት አምስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ አይዘነጋም።