የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት እስካሁን በአግባቡ መጠቀም አልቻሉም - ኢዜአ አማርኛ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት እስካሁን በአግባቡ መጠቀም አልቻሉም
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14/2013 (ኢዜአ) በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ ''በርካታ'' ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በአግባቡ እየተጠቀሙበት አለመሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በአዲስ አበባ አያካሄደ ነው።
ውይይቱ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ሂደት ላይ ያተኮረ ነው።
በዚህም ''በርካታ'' ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙሃን የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት በአግባቡ እየተጠቀሙበት አለመሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ ከተለያየ መገናኛ ብዙሃን የምርጫ ዴስክ ተወክለው የመጡ ሃላፊዎች እንደገለጹት ፓርቲዎቹ የተሰጣቸውን ነፃ የአየር ሰዓት ጊዜ እስካሁን በአግባቡ መጠቀም አልቻሉም።
የተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ከተሰጣቸው ነፃ የአየ ሰዓት ጊዜ ውስጥ እስካሁን የተጠቀሙት 51 ነጥብ 3 በመቶውን ብቻ መሆኑም ተገልጾል።
አስተያየታቸውን ከሰጡት ፓርቲዎች መካከል አንዳንዶቹ የተሰጣቸውን የአየር ሰአት በአግባቡ ያልተጠቀሙት ሚዲያዎቹ መልዕክቶቻችሁን ቀርፃችሁ ከ48 ሰዓት በፊት አምጡ በማለታቸውና የበጀት እጥረትም ስለገጠማቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከ2 ሳምንት በፊት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮችና ሃሳቦቻቸውን እንዲያቀርቡ ነፃ የጋዜጣ አምድ እና የአየር ጊዜ ድልድል ማድረጉ የሚታወስ ነው።