የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ የሚያካሂዱበት የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ የሚያካሂዱበት የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ ሆነ
ሚያዚያ 12 ቀን 2013 (ኢዜአ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ የሚያካሂዱበት የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ ተደረገ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁን አስታውሷል።
ይህንን ሂደት ለፖለቲካ ፓርቲዎች አቅርቦ ምክክር እንደተደረገበት ገልጾ፤ በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚቻል አመልክቷል።
በመሆኑም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድረገጽ እና በማህበራዊ ገጾቻችን በሚገኘው በዚህ http://www.nebe.org.et/ovrs ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) በመጠቀም መመዝገብ እንደሚቻል ገልጿል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይህንን የኦንላየን ምዝገባ ለተማሪዎች በማስተዋወቅ ትብብር እንዲያደርጉም ቦርዱ ጠይቋል።