ቀጥታ፡

ቻይና የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂን ገነባች

ሚያዚያ 12 /2013 (ኢዜአ) ቻይና በዓለም ትልቁን የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ በመገንባት የመጀመሪያ ስኬቶችን አስመዘገበች::

የሀገሪቱ የኢንድስትሪና የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቁት ሀገሪቱ በዓለም ትልቁን የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ማስፋፋት የሚያስችላትን ስራ በውጤታማነት መጀመሯን ገልጸዋል ::

ቻይና እኤአ እስከ የካቲት 2021 መጨረሻ ድረስ 7 መቶ 92 ሺህ የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ጣቢያዎችን መገንባቷን የኢንድስትሪና የመረጃ ቴክኖሎጂ ም/ሚኒስትር ሊዩ ሊዬሆንግ መናገራቸውን ሲጂቲኤን በዘገባው አስነብቧል፡፡

ሀገሪቱ እኤአ በ2021 ከ6 መቶ ሺህ በላይ የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂን ለመገንባት ያቀደች ሲሆን ትኩረቷንም ከኔትወርክ ሽፋን ተደራሽነት ወደ ፍጥነት እና ጥራት ማሳደግ ላይ እንዳዞረች ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም