ቀጥታ፡

ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና መድሓኒቶችና ቁሳቁስ እያከፋፈለ ነው

መቀሌ፤ ሚያዚያ 12/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ መቀሌ ቅርንጫፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና መድሐኒቶችና ቁሳቁስ እያከፋፈለ መሆኑን አስታወቀ።

የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ገብረማሪያም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የህክምና መድሐኒቶችና ቁሳቁስ እያከፋፈሉ ያሉት በክልሉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ 50 የጤና ተቋማት ነው።

ቀደም ሲልም በክልሉ ለሚገኙ የጤና ተቋማት መድሐኒቶችን ሲያከፋፈሉ እንደነበርም አውስተዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፋርማሲ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ገብረእግዚአብሔር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ የመድኒሐት አቅርቦትና ኤጀንሲ እንዲሁም ጤና ሚኒስቴር የአካባቢውን ህብረተሰብ  ከበሽታ ተጋላጭነት ለመጠበቅ እየሰጡ ላሉት ድጋፍ አመስግነዋል።

እየቀረበ ያለው መድሐኒት በቂ ባለመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም