ቤተክርስቲያኗ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ እና ብፁዓን ሊቀነ ጳጳሳትን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች - ኢዜአ አማርኛ
ቤተክርስቲያኗ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ እና ብፁዓን ሊቀነ ጳጳሳትን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች
አዲስ አበባ ሀምሌ 24/11/2010 የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ለመቀበል ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ቅዱስ ሲኖዶሱ ገለጸ። የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እንደገለጹት፤ በነገው ዕለት ወደአገር ቤት የሚገቡትን ብጹአን አባቶች በደማቅ ስነስርዓት ለመቀበል ዝግጅቱ ተጠናቋል። ብጹአን አባቶቹ ምዕመኑ በነገው ዕለት ከ5 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ እና በቅዱስ ካቴድራል በመገኘት እንዲቀበል አቡነ ዲዮስቆሮስ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሁሉም ሰው የቤተክርስቲያኒቱን ህግና ስነምግባርን በተከተለ መልኩ እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ተላብሶ በአቀባበል ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ወጣቶች በተገኙበት ቅዳሜ ሐምሌ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ደማቅ የአቀባበል ዝግጅት እንደሚኖር መገለጹ ይታወሳል።