ጠ/ሚ ዐቢይ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር በምርጫ ዙሪያ ተወያዩ

84

ሚያዚያ 7/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከክልል ፕሬዚዳንቶችና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር በምርጫ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

በዛሬ ውይይት የምርጫ ክንውኖችን እና ተግዳሮቶችን ለመገምገም በድጋሚ መገናኘታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁነት በአጥጋቢ ሁኔታ መከናወኑን ለማረጋገጥና መራጮች በቀሪው ጊዜ እንዲመዘገቡ ለማስቻል አቅጣጫዎችን መቀመጣቸውንም ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም ዜጎች በቀጣይ ቀናት የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ አበረታታለሁ ነው ያሉት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው።

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉም ነው ያሳሰቡት።

ከምርጫ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በየካቲት ወር የበይነ መረብ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም