የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

107

ሚያዚያ 7/2013 (ኢዜአ) የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ማሺዲሶ ሬቤካ ሞቲን በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል።

የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት፣ የጤናና የሰላም ጥብቅ ቁርኝት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትሯ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ገለጻ አድርገዋል።

አክለውም የአለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች አጋር የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች፣ በአጠቃላይ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ አዳጋች ሁኔታዎች በገጠማት ጊዜ ሁሉ ለሚያደርጉት እገዛ አመስግነዋል።

ዳይሬክተሯ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የመሰረታዊ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት ሽፋን ለበርካታ አመታት ሲከታተሉት የቆየ ጉዳይ መሆኑንና በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ ዘርፍ መሆኑ ለሌሎች ሀገሮች መልካም ምሳሌ እንደሆነ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲደርስ በመደረጉ በተባበሩት መንግስታት እና ሰራተኞቹ ስም አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም