ሀገር አቀፍ የምርምርና ጥናት ኮንፍረስ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ

78

ዲላ ሚያዚያ 6/2013 (ኢዜአ) "ምርምር ለማህበረሰብ ለውጥ " በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የምርምርና ጥናት ኮንፍረስ ዛሬ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው  ኮንፍረሱ በተለያዩ የትኩረት መስኮች ላይ  ከ77 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ወይይት እንደሚደረግባቸው  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ ገልጸዋል።

በሀገር ውስጥና ውጭ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልምዶችንና እወቀቶችን በመጠቀም የማህበረሰቡን ለውጥ ለማረጋገጥ ኮንፍረሱ  የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

በተለይ ዲላ ዩኒቨርሲቲው ተግባር ተኮር ምርምር በማድረግ የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ  ልምድና እውቀት ከኮንፍረንሱ  ለመቀሰም ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር አመልክተዋል።

የኮንፍረንሱ ተጋባዥ ምሁር  ዶክተር ጃርገ ፋንስስኮ  በበኩላቸው፤ የምርምርና ጥናት ግኝቶችን ወደ ህብረተሰቡ በማድረስ  ሕይወት ለመቀየር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ  ገልጸዋል።

የተመራማሪዎች የጥናት ግኝት ህብረተሰቡ ጋር ደርሰው የአመለካከትና የተግባር ለውጥ እንዲያመጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል።

በኮንፍረንሱ ከሀገር ውስጥና ውጭ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተጋበዙ ተመራማሪዎች፣  የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሃላፊዎች እንዲሁም የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ከዲላ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም