ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ ይገናኛሉ

ሚያዚያ 4/2013 (ኢዜአ) በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ባህርዳር ከተማ ይገናኛሉ።

ሊጉ ዛሬና ነገ አራት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።

በ18ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ10 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ እየተጫወቱ ይገኟል።

ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ደግሞ ወልቂጤ ከተማ ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ።

ነገ ደግሞ ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዳማ ከተማ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ይጋጠማሉ።

ሊጉን ፋሲል ከነማ በ41 ነጥብ እየመራ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በ33 ነጥብ ይከተላል፤ ባህርዳር ከተማ በ29 ነጥብ ሶስተኛ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ27 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት አቡበከር ናስር በ22 ግቦች ሲመራ፣ ሙጂብ ቃሲም በ17ና ጌታነህ ከበደ በ11 ይከተላሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም