ቀጥታ፡

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት እየሰራሁ ነው…የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

አዳማ፣ ሚያዝያ 4/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብልጽግና ጉዞውን ለማሳካት በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ አነስትኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ባንኩ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር በስምንት ማዕከላት 2ሺህ 500 ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች አገር አቀፍ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ዛሬ ስልጠውን በቪዲዮ መልዕክት ያስጀመሩት የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት ባንኩ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ለኢንተርፕራይዞቹ የፕሮጀክትና የሊዝ የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

“ይህም ዘርፉ ያሉበትን ችግሮች በመፍታት አገሪቷ ለተያያዘችው የብልጽግና ጉዞ የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ያስችለዋል” ብለዋል።

የባንኩ የአዳማ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ቦደና አለማየሁ በበኩላቸው በዚህ ለ5 ቀናት በተዘጋጀው 1ኛ ዙር ስልጠና ላይ የቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀት፣ ሂሳብ አስተዳደር፣ ንግድ ስራ አመራርና ገበያ ፍለጋ የመሳሰሉት ርዕሶች ላይ ግልጽነት ለመፍጠር የመስኩ ባለሙያዎች ልምዳቸውን ያካፍላሉ ብለዋል።

ልማት ባንክ ግን አሁን የጀመረውና ለአምራች ዘርፉ የሚሰጣቸው የብድር አገልግሎቶች "አገሪቷን ከድህነት አዙሪት ለማውጣት ከፍተኛ ድርሻ ያለውና ባንኩንም የሚያስመሰግን ነው" ብለዋል።

ሌሎች ባንኮችም ይህንን እንደ አርአያ ወስደው ሊከተሉ ይገባል ብለዋል አቶ ሽመልስ።

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ብቁ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀው ስልጠና ሁለተኛው ዙር በቀጣይ ወር እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ስልጠናው ከሚሰጥባቸው ማእከላት ደግሞ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጅማ፣ እና ጅግጅጋ ከተሞች ይጠቀሳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም