በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬና እና አትሌት ጌትነት ዋለ አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬና እና አትሌት ጌትነት ዋለ አሸነፉ
ሚያዚያ 4/2013 ( ኢዜአ) በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬና እና አትሌት ጌትነት ዋለ አሸነፉ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በማጠቃለያው ውድድር በበርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ሲጠበቅ የነበረው የ5 ሺህ እና የ1 ሺህ 500 ሜትር የወንዶችና የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ተካሂዷል።
በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ቀዳሚ ሆኖ ስታጠናቅቅ አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና መልክናት ውዴ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ከዚህ በፊት በመሰናክል ውድድር የሚታወቀው አትሌት ጌትነት ዋለ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።
በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር አትሌት ያሲን ሃጂ ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት መለሰ ንብረት ቀዳሚ ሆኖ ሲጨርስ ሳሙኤል አባተና መልካሙ ዘገየ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ለምለም ሃይሉ አንደኛ፤ ሂሩት መሸሻ ሁለተኛ፤ ፍሬወይኒ ሃይሉ ሶሰተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።
በሻምፒዮናው በወንዶችና ሴቶች አጠቃላይ ድምር ውጤት አንደኛ ደረጃን በመያዝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፤ መከላከያና ኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሁለተኛና ሶሰተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በዚህ ሻምፒዮና አሰልጣኝ ብርቱካን ቀጸላ ፣መቶ አለቃ ምትኩ እና ተፈሪ ጭብሳ ኮከብ አሰልጣኝ ተብለዋል።
እንዲሁም መኮንን ጤናው፣ ሽመልስ ዳዊት እና ተሾመ በቀለ በሻምፒዮናው ኮከብ ዳኞች ሆነው ተመርጠዋል።