ሉሲዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ የደቡብ ሱዳን አቻቸውን 11 ለ 0 አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
ሉሲዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ የደቡብ ሱዳን አቻቸውን 11 ለ 0 አሸነፉ
ሚያዚያ 03 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዋ ቡድን (ሉሲዎቹ ) በአቋም መለኪያ ጨዋታ የደቡብ ሱዳን አቻዎቻቸውን 11 ለ 0 አሸነፉ።
ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም የወዳጅነት ጨዋታ አካሂደዋል።
በዚህ ጨዋታ ላይ ሎዛ አበራ ብቻ 7 ጎሎችን ማስቆጠር ችላለች።
አረጋሽ ካልሳ ሁለት፣ ሴናፍ ዋቁማ አንድ፣ የደቡብ ሱዳኗ ተጨዋች ሎክሪ ዶርካ በራሷ ግብ ላይ አንድ ጎል በማስቆጠሯ ብሄራዊ ቡድኑ በድምሩ 11 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ትናንት ምሸት በተደረገው በዚህ ጨዋታ 81ኛው ደቂቃ ላይ በመብራት መጥፋት ምክንያት ተቋርጦ ቀሪው ዘጠኝ ደቂቃ ዛሬ ረፋድ ተካሂዷል።
እስከ 81ኛው ደቂቃ በነበረው ጨዋታ ዘጠኝ ጎል ያስቆጠሩት ሉሲዎቹ ዛሬ በተደረገው ቀሪ የዘጠኝ ደቂቃ ጨዋታ ተጨማሪ ሁለት ጎሎችን አክለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዋ ቡድን በፍፁም የበላይነት የደቡብ ሱዳን አቻውን 11 ለ 0 አሸንፏል።