የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ፌስቲቫል ነገ ይጀመራል

135

አሶሳ ፤ ሚያዚያ 01 / 2013 ( ኢዜአ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ፌስቲቫል ከነገ ጀምሮ በአሶሳ ከተማ እንደሚከበር የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወይዘሪት መስኪያ አብደላ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ለሁለት ቀናት የሚከበረው የፊስቲቫሉ ዓላማ በክልሉ የሚገኙ የሁሉንም ብሔር ብሄረሰቦችን ባህል በማስተዋወቅ ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ለማመቻቸት ነው፡፡

እንዲሁም ባህል ለሠላም ያለውን ፋይዳ በማጉላት የህዝቦችን አንድት በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡

የክልሉን ባህል የሚመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን የቱሪስት መዳረሻዎች የሚያሳዩ መጻህፍትም ይመረቃሉ፡፡

በክልሉ ባህል ቡድኖች ባህላዊ ሙዚቃ እና ጭፈራ ፣ የብሄረሰቦችን አመጋገብ እና አኗኗር የሚያሳዩ ዝግጅቶችም እንደሚኖሩም ተመልክቷል፡፡

ፌስቲቫሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሃገር አቀፍ ደረጃ የወጡ ፕሮቶኮሎችን በጠበቀ መልኩ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም